EXTERIOR

ሞኮሮኒ Recipe
Ingredients
► 1 ኩባያ ሞኮሮኒ 500ml ትልቁ የእርጎ ኩባያ
► 1 ሽንኩርት
► ትልቅ በደቃቁ የተከተፈ
► 1 ቲማቲም
► ትልቅ በደቃቁ የተከተፈ
► ዘይት
► ጨው
► ክኖር
► ከሪ ቅመም
► ኬችአፕ
► 2 እንቁላል
Process
■ 2 ኩባያ ወሀ በጨው ማፍላት
■ ሲፈላ ማካሮኒውን መጨመር
■ አልፎ አልፎ በሹካ ማገላበጥ እንዳይያያዝ
■ ለጥርስ ትንሽ ያዝ ሲያደርግ አውርዶ በወንፊት ማጥለል
■ መጥበሻ ላይ ዘይት ማጋል
■ ሽንኩርቱን መጨመር - ጠበስ ጠበስ ማድረግ
■ ቲማቲሙን መጨመር
■ ቅመሞቹን መጨመር
■ ኬችአፕ ጠብ ማድረግ
■ ውሀ ጠብ እያረጉ በደምብ ማቁላላት
■ በደምብ ከተቁላላ በኋላ የተቀቀለውን መኮሪን ጨምሮ ማዋሀድ
■ መጥበሻ ላይ ዘይት ጠብ አድርጎ ማጋል
■ እንቁላሉን መምታት
■ የተመታውን እንቁላል የጋለው መጥበሻ ላይ ማፍሰስ
■ እንቁላሉ ሲረጋ ከዳር ወደውስጥ እየገፉ ማፈርፈር