EXTERIOR

ሩዝ በዱባ Recipe
Ingredients
► 2 የውሃ ብርጭቆ እሩዝ
► 300 ግራም ዱባ
► 1 ፍሬ ቀይ ሽንኩርት (ትልቅ)
► 1 ቅጠል ላውሮ
► 1.5 ሊትር የ አትክልት ማጣፈጫ ሾርባ
► 1 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
► 2 ሾርባ ማንኪያ ዘይት
► ጨውና ቁንዶ በርበሬ
Process
■ ዱባውን አጥቦ፣ ልጦ በደቃቁ መቆራረጥ
■ የተቆራረጠውን ዱባ ውሃ ውስጥ ጨምሮ ማብሰል እና ማጥለል፣
■ የበሰለውን ዱባ ውሃ በብርጭቆ መዳመጥ
■ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት ልጦ፣ አጥቦ በደቃቁ መክተፍ፣
■ በድስት ውስጥ ዘይት አግሎ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርትና ላውሮውን በደንብ ማቁላላት፣
■ እሩዙን አጥቦ ወደ ሽንኩርቱ ጨምሮ መጥበስ ፣
■ የአትክልት ማጣፈጫ ሾርባ ጨምሮ ለ15 ደቂቃ ማብሰል፣
■ የተፈጨውን ዱባ ጨምሮ ለተጨማሪ 5 ደቂቃ ካበሰሉ በኋላ የገበታ ቅቤ፣ የስጎ ቅጠል፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ማውጣት እና ማቅረብ።