EXTERIOR

ኬክ ያለ ዘይትና የገበታ ቅቤ Recipe
Ingredients
► 150 ግራም ፉርኖ (3 የቡና ስኒ
► 150 ግራም ስኳር (3 የቡና ስኒ)
► 5 እንቁላል
► 1 ሾርባ ማንኪያ ቫኒላ
► ½ የሻይ ማንኪያ ጨው
Process
■ እንቁላሉን ነጩን አስኳሉን ለይቶ በተለያየ በጎድጓዳ ሳህን ማስቀመጥ፣
■ ስኳሩን ግማሹን ነጩ እንቁላል ውስጥ ግማሹን አስኳሉ ውስጥ ጨምሮ በደንብ ሁለቱንም መምታት፣
■ የተመታውን ነጭ እንቁላል ትንሽ ትንሽ እያደረጉ አስኳሉ ውስጥ እየጨመሩ ማማሰል፣
■ ቫኔላውን የተቀላቀለው እንቁላል ውስጥ ጨምሮ ማዋሃድ፣
■ የተዋሃደውን እንቁላል ውስጥ ዱቄትና ጨው ጨምሮ በደንብ ማደበላለቅ፣
■ የኬክ መጋገሪያውን ዘይትና ዱቄት መቀባትና ሊጡን መጨመር፣
■ በ 180 ዲግሪ በጋለ ኦቨን ውስጥ የኬክ መጋገሪያውን ከቶ ለ 20 ደቂቃ ማብሰልና የበሰለውን ኬክ አውጥቶ ማቀዝቀዝና ማቅረብ።