Choose your meal
ጎመን ቦልስ Recipe Ingredients ► 1 እስር የሃበሻ ጎመን
► 1 እንቁላል
► 1 የሾርባ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት
► 1 የሾርባ ማንኪያ የገብስ ዱቄት
► 1 የሻይ ስኒ በደንብ የበሰለ ቦለቄ
► 4 የቡና ስኒ የተፈጨ የዳቦ ዱቄት
► 1 ፍሬ ቀይ ሽንኩርት
► 1 ነጭ ሽንኩርት
► ½ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ አዝሙድ
► ½ የሻይ ማንኪያ እርድ
► ዘይት
► ጨውና ቁንዶበርበሬ
Process ■ ጎመን ቅጠል ሽንኩርት ነጭ ሽንኩርት በደቀቃቁ መክተፍ
■ የበሰለውን ቦለቄ መዳመጥ
■ እርድና ነጭ አዝሙድ በዘይት መጥበስ ነጭ ሽንኩርትና ቀይ ሽንኩርት መጨመር ማቁላላት ጎመኑን መጨመር ቦለቄውን መጨመር የገብስና የስንዴ እህሉን እንቁላል ጨው መደባለቅ ከዛ ማድቦልቦል
■ እንቁላልና ጨው መምታት የተድቦለቦለውን ጎመን ፉርኖ ዱቄት ላይ አንከባሎ ወደ እንቁላሉ ውስጥ እየነከሩ አውጥቶ ዳቦዱቄቱን ማስነካት ከዛ ጠብሶ አቀዝቅዞ ማቅረብ

