EXTERIOR

ሎሚ ፓስታ Recipe
Ingredients
► 1/2 ኪሎ ፓስታ
► 6 ዛላ ሚጥሚጣ
► 6 ፍሬ ሎሚ
► 4 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
► 4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
► ጨውና ቁንዶ በርበሬ
Process
■ በትልቅ ድስት ውስጥ 2 ሊትር ውሃና ጨው አፍልቶ ፓስታውን መቀቀልና ማቀዝቀዝ፣
■ ሎሚውን ለ2 ሰንጥቆ መጭመቅ፣
■ ነጭ ሽንኩርት ልጦ፣ አጥቦ በስሱ መክተፍ
■ በመጥበሻ ዘይት አግሎ ነጭ ሽንኩርቱንና ሚጥሚጣውን ማቁላላትና፣ ግማሹን የተጨመቀ ሎሚ መጨመር፣
■ የተቀቀለውን ፓስታ መጥበሻ ላይ ጨምሮ በደንብ ማደባለቅና የቀረውን ሎሚ፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ አደባልቆ አውጥቶ ማቅረብ።